cover image: Peace Research Facility - የሴቶች ሚና በኢትዮጵያ ክልልላዊ እና አገር አቀፍ

20.500.12592/b5k1kh

Peace Research Facility - የሴቶች ሚና በኢትዮጵያ ክልልላዊ እና አገር አቀፍ

6 Nov 2023

Peace Research Facility የሴቶች ሚና በኢትዮጵያ ክልልላዊ እና አገር አቀፍ የሰላም ሂደቶች ገሊላ ታፈሰወርቅ ጥቅምት 2016 በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሴቶች የተለያዩ የፖለቲካ፣ የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ተግዳሮቶች ያጋጥሟቸዋል። በሌሎች አገሮች እንደሚታየው ሁሉ፣ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ግጭቶች ሴቶችን ተመጣጣኝ ላልሆኑ ስቃዮች፥ ጥቃቶችና እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ያጋልጧቸዋል። ይህም የሰላምን አስፈላጊነት የሚያጎላ ሲሆን፣ የሴቶችን እና የልጃገረዶችን ደኅንነት ከማረጋገጥ ባለፈ የሴቶችን መብት ከማክበር ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን የሰላም ሂደቶችን ዘላቂነት እና ህጋዊነት ለማረጋገጥ ትርጉም ያለው የሴቶ. [...] በ2019) ዴስትኒ ኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚመራ የውይይት ባህልን በፖለቲካ አውድ ውስጥ በማስፋፋት የተለያየ አመለካከት ያላቸውን የፖለቲካ እና የፖለቲካ ያልሆኑ ተዋናዮችን በአንድ ላይ ለማሰባሰብ ያለመ ሀገራዊ የውይይት መድረክ አስተዋውቋል። በዚሁ ሂደት ውስጥ ተሳታፊዎችን ለመለየት ‘የብዝኃ መስፈርት ዳሰሳ’ ተካሂዶ በጥቅምት ወር 2013 (እ.ኤ.አ. [...] 2020) ሁሉን አቀፍ አገራዊ የምክክር ውጥን - ኢትዮጵያ (ማይንድ-ኢትዮጵያ) ተመስርቷል።3 ሁሉን አቀፍ አገራዊ የምክክር ውጥን - ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ሴቶች የሚመሩ ድርጅቶችን እንደ አንድ የተለያ ፍላጎት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍል በመመልከት ተሳትፏቸውን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል። በ2014 (እ.ኤ.አ. [...] በ2022) አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ሂደቱን እንዲመሩ 11 ኮሚሽነሮች ተሾሙ።4 ይህ አግባብ ባለው ተቋም ውስጥ የሰላም ጥረቶችን ከማጠናከር አንፃር እንደ አዎንታዊ እርምጃ ሊወሰድ ቢችልም፤ በአንዳንዶች ግን ጾታን ያማከለ፣ በጥናት ላይ የተመሰረተ እና ማኅበረሰቡን መሰረት ያደረገ የሰላም ሂደት ከመሆን ይልቅ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትን ማበረታታት እንደሆነ ይታያል።5 ሴቶች እና አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፤ ድብልቁ ቦርሳ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሥርዓተ-ፆታን አካታች በመሆን ረገድ ስኬቶች ቢኖሩትመ፣ ለአንዳንድ ትችቶች ግን ተዳርጓል። በአዎንታዊ ጎኑ፣ በሀገራዊ ምክክር ኮ. [...] በ2021/2022) አገራዊ የምክክር ሂደት ከመጀመሩ ጎን ለጎን በክልሉ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት የተቀናጀ ጥረት ተደርጓል። ለዚህም ባህላዊ የሰላም ማስፈን ጥረቶችን ከመደበኛ የክልል ውይይቶች ጋር ማዋሃድ በዋነኝነት ይጠቀሳል።8 እነዚህ መደበኛ ጥረቶች በክልሉ መንግስት እና በክልሉ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች መካከል በተደረጉ ተከታታይ የሰላም ስምምነቶች አማካይነት ቅርፅ ይዘዋል።9 በአንፃራዊ መልኩ የግጭት መጠኑ ቢቀንስም በክልሉ ለተከሰቱት ሁከት መንስኤዎች በቂ መፍትሄ ባለማግኘቱ ተደጋጋሚ ግጭቶችና የሰብአዊ 6 ከሴቶች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የጋራ ምክር ቤት ተወካይ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ, ሐምሌ 17፣ 201.
Pages
4
Published in
Kenya